ወደ ሁዲንጌ ቤተ-መጻሕፍት እንኳን ደህና መጡ! ከሁዲንጌ ቤተ-መጻሕፍት መጽሐፍ ለመዋስ፥ አንድ የቤተ-መጻሕፍቱ ካርድና አንድ ማለፊያ ኮድ ያስፈልጎታል። ካርዱን በነጻ ማግኘት የሚቻል ሲሆን፥ በስድስቱም ቤተ-መጻሕፍቶቻችን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በካርዱ መጻሕፍት፥ ፊልሞች፥ መጽሔቶች፥ ሲዲዎችና ኤ-መጻሕፍት መዋስ ይችላሉ። ከቤተ-መጻሕፍቱ ለመዋስ ክፍያ አይጠየቁም። የቤተ-መጻሕፍት ካርድ ለማውጣት፥ መጀመሪያ እኛ ዘንድ መጥተው መመዝገብ ይኖርብዎታል። ድረ- ገጻችን ላይ በሚገኘው ቅጽ ላይ በመሙላት ወይም በአካል ቤተ-መጻህፍቱን ሊጎበኙ ሲመጡ፥
መመዝገብ ይችላሉ። ካርድ ለማውጣት ጎራ ሲሉ መታወቂያዎን መያዝ አይዘንጉ።
መጻሕፍትና መጽሔቶች በብዙ ቋንቋዎች
በሁዲንጌ ቤተ-መጻሕፍት የተለያዩ፥ የብዙ ቋንቋዎች መጻሕፍትና መጽሔቶች ያገኛሉ። በድረ-ገጻችን ላይ ”Pressreader” የሚለውን የድረ-ገጽ ግልጋሎት በመጠቀም፥ በመላ ዓለም የሚዘጋጁ ዕለታዊ ዲጂታል ጋዜጦችን ማንበብ ይችላሉ።
ስዊድንኛ መለማመድ ከፈለጉ በቀላል የሚነበቡ መጻሕፍትና የቋንቋ ኮርሶች አሉን። ይጠይቁን፥ሰራተኞቻችን የሚፈልጉትን እንዲያገኙ ይተባበርዎታል።
ኮምፒዩተሮችና ሽቦ-የለሽ ኢንተርኔት
የቤተ-መጻሕፍቱ ካርድ ካለዎት በሁሉም ቤተ-መጻሕፍቶቻችን ሊጠቀሙባቸው የሚችሉኮምፒዩተሮችና ሽቦ-የለሽ ኢንተርኔት አሉን።
መዋስና ለመዋስ ተራ መጠበቅ
ለምን ያህል ጊዜ መዋስ እችላለሁ?
መደበኛው የውሰት ጊዜ ዐራት ሳምንታት ነው፥ ይሁን እንጂ ከዚህ ለየት ሊል ይችላል። ለምሳሌ ፊልሞችንና በጣም ተነባቢ የሆኑ መጻሕፍትን በተመለከተ የውሰት ጊዜው ሊያጥር ይችላል።በሚዋሱበት ጊዜ የሚወስዱት ደረሰኝ ላይ፥ የሚመሉስበት የመጨረሻው ቀን አለ።
ዘግይቼ ብመልስ ምን ይከተላል?
እንዲያ ከሆነ የመዘግየት መቀጮ ይጠየቃሉ። የመቀጮው መጥን በተዋሱት ቁስና የዘገዩበት ጊዜ
ርዝመት ላይ የተመሰረተ ይሆናል።
እንዴት ነው በድጋሚ የምዋሰው?
በካርድዎና በማለፊያ ኮድዎ አማካኝነት ድረ-ገጻቸን ውስጥ በመግባት ወይም ከቤተ-መጻሕፍቶቻችን አንዱ ጋር በመደወል በድጋሜ መዋስ ይችላሉ። በአብዛኛው ሁለት ጊዜ በድጋሚ መዋስ ይችላሉ፥ ይሁን እንጂ ከዚህ ለየት የሚልበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ፥ ሰው ሊዋሳቸው የሚጠብቃቸውን ፊልሞችንና መጻሕፍት በድጋሚ መዋስ አይቻልም።
በውሰት የወጣን መጽሐፍ ለመዋስ፡ ተራ መጠበቅ እችላለሁን?
አዎ! ይችላሉ። በሁዲንጌ ቤተ-መጻሕፍት መጽሐፍ ለመዋስ ተራ መያዝ ምንም አያስከፍሎትም።ከሁዲንጌ ቤተ-መጻሕፍት ውጭ መጻሕፍት ማዘዝ እችላለሁን? አዎ! ይችላሉ። ከሁዲንጌ ኮምዩን ውጭ መጻሕፍት ማዘዝ 10 ክሮኖር ያስከፍላል።
ማወቅ የሚገባዎ ሌሎች የውሰት ድንቦች፡-
- ከ18 ዓመት በታች የሆነ፥ የቤተ-መጻሕፍት ካርድ ለማውጣት አሳዳጊው መፈረም ይኖርባቸዋል።
- ለተዋሱት መጻሕፍት ሁሉ ሐላፊነት አለብዎት።
- ልጆች ለተዋሱት ሁሉ፥ ሐላፊነቱ የአሳዳጊው ነው።
- የተዋሱትን በማንኛውን ቤተ-መጻሕፍታችን መመለስ ይችላሉ።
- የተዋሱትን በጊዜ የመመለስ ሐላፊነት አለብዎት።
- የአንድ መጽሐፍ መመልሻ ጊዜ ካለፈ የሚጠየቁት ክፍያ ይኖራል።
- ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ምንም አይከፍሉም።
- መጽሐፉን ካልመለሱ ቤተ-መጻሕፍቱ ዋጋውን እንዲከፍሉ መጠየቂያ ቅጽ ይልክልዎታል።
- የዘገየውን መጽሐፍ ከመልሱ ግን የመጽሐፉን ዋጋ መክፈል አይጠበቅቦትም። ይሁን እንጂ በመካያው የመዘግየት መቀጫ ሊጠየቁ ይችላሉ።
- የተዋሱት መጽሐፍ በእጅዎ እያለ ከተበላሸ፥ መተካት ይኖርብዎታል።
- ለጠፋ መጽሐፍ ዋጋውን ከከፈሉ በኋላ መጽሐፉን ካገኙት፥ ገንዘብዎ አይመለስሎትም።
- ከ100 ክሮኑር በላይ እዳ ካለብዎት፥ መጽሐፍ መዋስም ሆነ ለመዋስ ተራ መያዝ አይችሉም።ዕዳዎን ከከፈሉ በኋላ ግን እንደ ቀድሞው መዋስና ለመዋስ ተራ መያዝ ይችላሉ።